×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:50

ሥራ ሥራ፣ ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት ትሆናለች Featured

Rate this item
(0 votes)

የመጽሐፍ ግምገማ

ሥራ ሥራ፣ ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት ትሆናለች

ደራሲ፦ ደመወዝ አበበ

የታተመበት ሥፍራ፦ አዲስ አበባ

የታተመበት ዘመን፦ 2002 ዓ.ም.

አታሚ፦ አልተጠቀሰም

የገጽ ብዛት፦ 210


“ሥራ ሥራ” የሥራን ክቡርነት ለማስረዳትና በአንጻሩ የስንፍናን ባህል ቀርፎ በአገር መኩራራትን ለማዳበር ታስቦ የተጻፈ መጽሐፍ ነው [“ሥራ … ሥራ … በአገርህም ኩራ” እንዲል]። መጽሐፉ በ17 [አጫጭር] ምዕራፎች ተከፋፍሏል። ኢትዮጵያን የዳቦ ቅርጫት እንዳትሆን የተጋረጡባትን ምክንያቶች ይዘረዝራል። የተሳሳተ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ፣ ባቋራጭ መክበር፣ ሥራን መናቅ፣ ራስን መካብ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው ይላል። ደራሲው ይህን መጽሐፍ ሲጽፍ የሌሎች አስተዋጽኦ እንዳለበት በመግለጽ አንባቢውን ለማደፋፈር ሞክሯል።

ደራሲው ገጠመኞችና ሰሞነኛ አባባሎችን እየደጋገመ፣ ችግሮች ባይጋረጡባት ኖሮ ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት በሆነች ነበር [ወይም በእንግሊዝኛ እንደ ተመለከተው “የብልጽግና ቀንድ” ትሆን ነበር] ይለናል። አገላለጹ ግልጽ ሆኖ ሳለ፣ የእንግሊዝኛ ቃላት ጣልቃ ማስገባት ለምን እንዳስፈለገ አልገባንም፤ በተለይ ምዕራፍ 6፣ ገጽ 89-90]። ይህን መጽሐፍ እንደ ሌሎች መጻሕፍት መገምገም አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተነዋል። የመጽሐፉ አደረጃጀት በ“ራስ ማሻሻያ” መጻሕፍት መልክ ነው። አገራችን የዳቦ ቅርጫት እንዳትሆን የተገጠገጡባትን ኃይላት በመዘርዘር ላይ ከማተኮሩ የተነሣ ለዋነኛ ጉዳዮች እልባት መስጠት ተስኖታል። [ለምሳሌ፦ ስለ ጦርነት፣ ምን ዓይነት መንግሥታዊ አስተዳደር ምን አስተዋጽዖ እንደሚኖረው አላብራራም። ምዕራፍ 13 ይመልከቱ]። በመጨረሻ፣ “እንዲህ እንጂ እንዲህ መሆን የለበትም” የሚሉ ግብታዊ መፍትሔዎችን ሰጥቶናል። ለዚህም ማብራርያ መልስ መስጠት ይኖርበታል። ያልተጠየቀ አሳብና አባባል ሲቆይ መደበኛ ይሆናል። አልፎም፣ የአንድን የእምነት ክፍል መወከል ይጀምራል።

ደራሲ ደመወዝ እስካሁን ሦስት መጽሐፍት የጻፈ ሲሆን ለሕትመት ደግሞ አራት እንዳዘጋጀ ተመልክቷል። ለማንበብና ለመጻፍ ጥረቱና ትጋቱ ሊመሰገንና ሊበረታታ ይገባል። ከማበረታቻ መንገዶች አንዱ ደግሞ ለንባብ ባበቃቸው ላይ መወያየት ነው። ተጠያቂነት እንዳለ፣ በጥቃቅኑ ሳይቀር ጥንቃቄ አለማድረግ የሚያስከትለውን መዘዝ አንባቢና ደራሲ መገንዘብ  ይኖርባቸዋል። ስለዚሁ መጽሐፍ ቀጥሎ የተመለከቱትን አሳቦች እንመልከት፦

1.  መጽሐፉ ጅምላ ድምዳሜ ይታይበታል።

·         “ሞትን የምንፈራው ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ስለማናምን ነው?” [ገጽ 42]

·         ጃፓኖች ከሚያመልኩት አምላካቸው ዋነኛው ቡድሃ “ግቡና ሃሳቡ መሥራት ሳይሆን ተኝቶ መቀለብ ነው” ተብሏል [ገጽ 49]። አምላካቸው እንዲህ ከመሰለ እንዴት በሥልጣኔ ሊገሠግሡ ቻሉ?

·         “በፈሊጥ ካልገባህ በፍልጥ ይገባሃል” የሚለው አባባል ፍልጥ መጠቀም ለሚቀናቸው ድፍረት አይሰጥም? በአምላክ አምሳል የተፈጠረን ስብእና ረግጠው ለመግዛት የሚዳዳቸውን ክንድ ለማበርታት፣ ለሚረገጠው ተረግጦ መገዛት ልክ ነው ማለት አይመስልም?

2.  የማይነጻጸሩትን ያነጻጽራል። ኬንያና ሱዳን ቅኝ ተገዝተዋል፤ እኛ በአንጻሩ ቅኝ አልተገዛንም። በተማረ የሰው ኃይል ከኛ ቢበልጡ ለምን ይደንቃል? እንዴት ከኋላ ተነሥተው ቀደሙን ማለትስ ይቻላል? እኛ ሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ እያለን፣ እስራኤል እንዴት በ57 ዓመት ውስጥ ቀደመችን ማለት የሕዝቦችን ታሪክ ሂደት አለማጤን አይደለም ወይ? [ሕዝበ እስራኤል በ1940 ዓ.ም. ከተበተኑበት ተሰባስበው እንደገና ተቋቋሙ]። እስራኤል አንድ ሕዝብ ነው፣ ሃይማኖቱ አንድ ነው፤ ቁጥሩ አናሳ ነው [ብዛቱ ዛሬ የኛዎቹን ፈላሻ ጨምሮ ወደ 6 ሚሊዮን ይጠጋል]። እንደ ገና አንሠራርታ እንድትቋቋም ያደረጉት በዓለም ዙሪያ ተበትነው የኖሩ ከሃብትና ከዕውቀት ዓይነት ሳይቀር ያካበቱት ዝርያዎቿ ናቸው። በዚህ ላይ የህግ የበላይነት የሚገዛበት፣ ብሔራዊ አንድነትና ዲሞክራሲያዊ ነጻነት የሠፈነበት ማህበረሰብ ነው። እኛም የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ አለን እንበል እንጂ ዛሬ በምንገኝበት ሁኔታ ውስጥ አልነበርንም። ይልቅ ውጭ የተበተነው የተማረው የአገራችን ሕዝብ ወደ አገሩ ተመልሶ ያለሥጋት መኖር ቢችል ምን ለውጥ ያስገኝ ይሆን? ማለት ያዋጣ ይሆናል።

3.  ውስብስቡን እንደ ቀላል ያያል፤ ለውስብስብ ጉዳይ ግልብ የሆነ መፍትሔ ያቀርባል [ቁ.6ን በተጨማሪ ይመልከቱ]። “ተባብረን እንሥራ” ማለት መልካም ነው፤ ተባብረን እንዳንሠራ ያደረገንን ጠንቅቆ መለየትና ተባብረው የሚሠሩ ለምን ተባብረው ሊሠሩ እንደቻሉ ማገናዘብ ያሻል። “በግ ከተገዛ ቅርጫው ቢቀርስ” ጥሩ አባባል ነው። ሆኖም ቅርጫ ማህበራዊ ይዘት እንዳለው መዘንጋት የለብንም፤ ቅርጫ ጎረቤት ከጎረቤት እና ወዳጅ ከወዳጁ ጋር የሚተጋገዝበት ማህበራዊ እሴት የሚጋራበት ሥርዓት ነው። “ከልመና አስተሳሰብ እንውጣ” ማለት ቀላል ነው። አገራችን በተለይ ባለፉት ሃያ ዓመታት ከሠላሳ ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ተደርጎላታል። [በደርግ ዘመን ሶሻሊስት መንግሥት ስለ ነበረና ይህንኑ መንግሥት ለመጣል ከነበራቸው ዓላማ  የተነሳ ምዕራባውያን ለድርቅና ለረሃብ ከሚሆን ቁሳቁስ ያለፈ እርዳታ ለመስጠት እምብዛም ደንታ አላሳዩም ነበር።] ሆኖም፣ ደራሲው ከዚህ አኳያ “እርዳታ ሲለመድ የመሥራት ፍላጎት እየቀነሰ ይሄድና ይጠፋል …ልመና ጥገኛ ያደርጋል …ማንነትን ያሳጣል” ያለው እውነትነት አለው።

4.  በጎ ምኞትን ከሚታየው እውነታ አይለይም። አገርን መውደድ መልካም ነው። አገላለጻችን ይለያይ እንጂ ሁላችንም አገራችንን እንወዳለን። ለአገርና ለወገን በጎ መመኘትም እንደዚሁ መልካም ነው። ነገሩ ግን እንኳን በአገር ደረጃ በቤተሰብም ውስጥ ያለውን ማስማማት አስቸጋሪ ነው እኰ። ለአገራት ደግሞ ከሌሎች አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማስማማት ቀርቶ ማቀራረብ እጅጉን ከባድ ነው። ከግለሰብ ጀምሮ እስከ አገራት የሚታየው ሁሉም ራሱን ለማስቀደም መጣሩና ያልታሰቡ ብዙ መሰናክሎች መኖራቸው ነው። እስቲ እነዚህን አባባሎች እንያቸው፦

ሀ. “ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት መሆኗ ቀርቶ የዳቦ ቅርጫ ውስጥ ገብታ ኖራለች። ከእንግዲህ ግን እንዲህ አይሆንም።” [ገጽ 11] ለዚህ ግብታዊ አባባል የታሪክ ማስረጃ አለ?

ለ. “ያኔ [በደርግ ዘመን] በሁሉ ነገር የዓለም መጨረሻ የሆነችው ኢትዮጵያ የዓለም መጀመሪያ ትሆናለች ብዬ እገምታለሁ … በዓለም ላይ ያለን የድህነት ታሪክና መታወቂያችንም ተረት ሆኖ ይቀራል” [ገጽ 11-12]። በደርግ ዘመን ኢትዮጵያ “በሁሉ ነገር የዓለም መጨረሻ ነበረች?”

5.  ደራሲው በመገናኛ ብዙኃን የሚሰማውን የሚያስተጋባ ይመስላል። ወይም ነገሮችን ለማጣራት ካለመፈለግ የመነጨ ሊሆን ይችላል። በደርግ ዘመን “ይውደም፣ ይውደም” “ወደ ፊት” “እናት አገር ወይም ሞት” “እጥፍ ድርብ እናመርታለን” የመሳሰሉ ቃላት እንደ ነበሩ ሁሉ ማለት ነው። ደራሲው፣ ተቀማጭነታቸው ውጭ አገር የሆነ ዜጎች፣ አገር ቤት ኢንቬስት ያድርጉ ይላል [ለምንድነው ጉትጎታ ያስፈለገው ብሎ አይጠይቅም]። ዓባይን ለአገር ጥቅም እናውል፤ ድህነትን እናጠፋለን ይላል። ድህነትን ማጥፋትማ የዓለም ባንክ ከሃምሳ ዓመት በፊት መፈክር አንግቦ ተነሥቶ ነበር፤ በዓለም ዙሪያ ዛሬ የሚታየው ድህነት ግን ያኔ ከነበረው አልተሻለም። ወደ እናት አገራችሁ ኑና አብረን እንሥራ፣ ይላል። በምድር ዙሪያ የተበተነው ዜጋ እውን ወደ አገሩ መመለስ ጠልቶ ነው? ለምንድነው ከደርግ ዘመን ይልቅ ሕዝቡ አገሩን ጥሎ ለመሄድ የሚፈልገው? ለምንድነው በሲና እና በሊብያ ምድረ በዳዎች የሚቅበዘበዘው?ወደ የመን ለመሻገር ማዕበሉ ላይና ታች የሚያዳፋውና የሚበላው? በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የወጣው እንዳለ ተመልሶ አገር የሚገባ የነበረው ለምን ነበር? ታሪክ አለማገናዘብ የደራሲ ደመወዝ መጽሐፍ ዋነኛ ድክመት ነው። ለምሳሌ፦ ደርግ፣ “እናት አገር ወይም ሞት” ወይም “የምርት ዘመቻ ግቡን ይመታል” ወይም “ከጓድ ሊቀመንበር ጋር ወደ ፊት” “እናት አገራችንን እንዲህና እንዲህ እናደርጋታለን” የመሳሰሉትን ወና መፈክሮች ማስታወስ ለመጽሐፉ ጥንካሬ በሰጠው ነበር። በሌላ አነጋገር፣ መንግሥታት ሁሉ የሕዝብ ቀልብ ለመሳብ የሚቀይሱት መርሆ ይመሳሰላል ለማለት ነው።

6.  እውነታን መካድ አይቻልም። ከእምነት ውጭ ያሉ ይደንሳሉ፤ ይሰክራሉ። አማንያንም ወሬ ያወራሉ፤ ይነታረካሉ። ድህነት በሰው ታሪክ ውስጥ የጠፋበት ዘመን የለም። የማይገኝበትም ማህበረሰብ የለም። ዓለምና ምኞቱ ክርስቶስ መጥቶ እስኪሽራቸው ድረስ ይኖራሉ። የኃጢአት ጠባሳ ጌታ እርሱም ክርስቶስ መጥቶ ሁሉን አዲስ እስከሚያደርግ ድረስ ውጤታቸው አይወገድም። ህመም፣ ለቅሶ፣ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ሞት ወዘተ ይቀጥላሉ። በክርስቶስ የሚያምኑም በዓለም ናቸውና መከራ አለባቸው። ልዩነቱ በክርስቶስ ላመኑት የዘላለም ተስፋ አላቸው፤ በደህንነት ይኖራሉ፣ ጸጋ አለላቸው፣ ዓለም የማይሰጠውን ሰላም አላቸው።

7.  አባባሎች ትውልድ ሠፈራቸውን ለቀው ጥገኛ በሆኑበት አገር ቀድሞ ከነበራቸው ውጭ ያልታሰበ ትርጉም ሊቀዳጁ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ “በአንድ አህያ ከሚመሩ መቶ አንበሶች ይልቅ፣ በአንድ አንበሳ የሚመሩ መቶ አህዮች ያስፈሩኛል” የሚል አባባል ተመልክቷል [ገጽ 159]። ይህን መሰል አባባል ደራሲው ከራሱ ያመንጫቸው ወይም ከእንግሊዝኛው ይተርጉማቸው አልገለጸም። “የተወረወረበትን ድንጋይ ቤት ይሠራበታል” የሚለው ለምሳሌ በእንግሊዝኛ የተለመደ አባባል ነው። “አገርስ የጋራ ነው፣ ድህነት የግል ነው” የሚለው አባባል “አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው” ከሚለው ጋር ይመሳሰላል። እውን ግን ደራሲው እንዳለው ድህነት የግል ነው? እንኳንስ ድህነት ሃይማኖትም እንኳ በመሠረቱ የግል አይደለም። የሚጋራ ከሌለ ሃይማኖት ለዛና ሥርዓት አይኖረውም። ከሁሉ አስቀድሞ ሰው ማህበራዊ ፍጥረት መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።

መደምደሚያ፦

በቀላል አማርኛ መጻፉ፣ በየመጽሐፉ ምዕራፎች መካከል እና መደምደሚያ ላይ የተመለከቱት ጥቅሶችና ማጠቃለያ አሳቦች መጽሐፉን ተነባቢ አድርጎታል። አንዳንዶቹም አባባሎች አንባቢውን ከማሳሰብ አልፈው ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ሳያመካኝ እንዲታትር ይጋብዛሉ። ለምሳሌ፦ “ታዲያ አሁን እኔ ብሞት ምን ተብሎ ነው የሚጻፍልኝ?” [ገጽ 37] በሌላ አንጻር፣ በኦርቶዶክስ እና በወንጌል አማንያን ዘንድ ስለ ሥራ ያለውን የተዛባ አመለካከት ገልጾ ሲያበቃ፣ የእስልምና ተከታዮችንና ከዚህ ሁሉ ውጭ ያሉትን በጥናቱ ውስጥ አላካተተም።

ሥራ ጥሪ ነው፤ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሯል፤ የተፈጠረው እንደ ፈጣሪው እንዲፈጥር፣ እንዲያበጃጅ፣ እንዲሠራ ነው፤ እያለ በአውሮጳውያን ዘንድ ስለ ሥራ ያለውን ነገረ-መለኮታዊ መረዳት ይጠቅሳል። በእኛም አገር በየገዳማቱ “ጸሎትና ሥራ” ተጣምረው መገኘታቸውን አልጠቀሰም። ደራሲ ደመወዝ በመጽሐፉ ውስጥ እንዳሳሰበን የራሳችንን ለይተን አለማወቅ ጉዳት ነው። የራሳቸውን ቀለም አቅልመው ብራና ላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማዘጋጀታቸው፣ ገዳማትና አድባራት በዛፍ አጠድና ለመብል በሚሆኑ ተክሎች መሞላታቸው፣ ሕይወታቸው አንድ ወጥ እንጂ፣ ይህ መንፈሳዊ፣ይህ ሥጋዊ አለመባሉ፣ ሥራ የአምልኮ አንድ ገጽታ መሆኑ፣ ሁለንተናቸው እግዚአብሔርን ለማገልገል መሰጠቱ ዛሬ ለሚናፈሰው ግለኛ ክርስትና እርምት ይሰጣል ብለን እንገምታለን። አገር-በቀል የሆኑ በጎ የሥራ ባህሎችን መጥቀሱ፣ ለዚህም መሠረቱ ከቤት እንደሚጀምር፣ በተለይም የእናቶቻችንን ጥረት ማመስገኑ ጥሩ ትዝብት ነው [ገጽ 13]።

የ66ቱ አብዮት በፈነዳ ማግሥት፣ ሃይማኖተኞች ሥራ አይሠሩም፤ ሃይማኖት ሥራ ፈት ያደርጋል ይባል ስለ ነበረ ቤተክርስቲያን ስለ ሥራ አበክራ ትምህርት ለመስጠት ተገድዳ ነበር። በአብዮቱ መጀመሪያ ላይ [ላብ አደሩን] ወዛደሩን ለማንገሥ ሲባል “ሥራ” ማለት በእጅ የሚሠራው ነው ተብሎ ነበር። የአእምሮ ሥራ ሥራ እንዳልሆነ ይቆጠር ነበር። ኋላ ደግሞ ካድሬው ሲፈለፈል አእምሮአዊ “ርዕዮተ ዓለም” ወይም “ቲዎሪ” ተራውን ንጉሥ ሆነ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ሠራተኛነታቸውን ለማስመስከር ሲሉ ከእምነት እስከ መፈናቀል ደርሰዋል። ዛሬም ሥራ አጥነት ቢወገድ ሥራ በመጥላት ሳይሆን ሥራ በማጣት የቤተክርስቲያን ደጅ ሲያጣብብ የኖረው ጥሎ እንዳይፈረጥጥ ያሠጋል። ወቅቱ ዓለማዊነት ቤተክርስቲያን ውስጥ ተደላድሎ የሚታይበት ወቅት፣ የቤተክርስቲያንን ሥልጣን የሚቀናቀኑ ተጠሪነት የጎደላቸው ግለኛ “ሚኒስትሪዎች” የበዙበትም ዘመን በመሆኑ በዓለም ውስጥ ያለው ሁኔታ ሲመቻች የባሰ ችግር መከሰቱ የማይቀር ነው። ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። “ሥራ ሥራ፣ ትምህርት ትምህርት” ማለት መልካም ቢመስልም አክርረን ከያዝነው ወጥመድ ሊሆን ይችላል።

ፋሺስት ጣልያን የፈጃቸው ምሑራንና የሕዝብ መሪዎች፣ ደርግና ኢሕአዲግ የዜጎችን ተሳትፎ በማጥበባቸው አገሪቱን ሊያገለግሉ ሲገባና ሲችሉ በእስር፣ በስደት የሚገኙ ባላስፈላጊ ጦርነቶች የረገፈው ግብረ ኃይል ያደረሰው ቀውስ በዚህ ጽሑፍ ሊታከል ይገባል። በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ በቤተክርስቲያን የሥራን ክቡርነት ማስተማር አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው። ደግነቱ በውጭው አገር ሳይሠሩ፣ የሚሠሩትንም ሳያማርጡ መታገል ውዴታ አይሆንም። አገር ቤት በሥራ ንቀት ያሞላቅቅ ይሆናል። ውጭ አገር ግን ሞዛዛነት ደህና ሰንብች ነው!

“ሥራ ሥራ” ብዙ ውይይት የሚያሻው መጽሐፍ ነው። ደራሲ ደመወዝ ይህን አሳሳቢና ጠቃሚ ጉዳይ ማቅረቡ ሊያስመሰግነው ይገባል። በሚቀጥለው ሕትመት እነዚህን በከፊሉ ያነሳናቸውን ነጥቦች ያብራራል ብለን እንገምታለን፤ ወይም በሌላ ጽሑፍ ላይ ጥንቃቄ በተሞላበት ስልት ጥናቱን ያካሄዳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በተረፈ እግዚአብሔር ምድራችንን እና ሕዝቦቿን ይባርክ። ሕዝብ የሚያከብሩ፣ በጉቦ የማይደለሉ፣ ፍትህና ሰላም የሚወዱ፣ ርኅራኄና ማስተዋል ያላቸውን መሪዎች አይንሳን።

በመጨረሻም፣ ዘጠኝ የተለያዩ አብያተክርስቲያናት መሪዎች [ሁሉም ወንዶች] ለደራሲው ትረካ ድጋፍ ከመስጠት አልፈው አንባቢውን በዚህ አሳብ ለማበረታታት አስተያየት ሠንዝረዋል። በዚሁ በአገር አቀፍ ምርጫ ሰሞን የአብያተክርስቲያናት መሪዎችን፦ “ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ምን ትመስላለች?” “እግዚአብሔር ስለ ኢትዮጵያ ምን ይላል?” “የእግዚአብሔር ሀሳብ ለኢትዮጵያ በአገልጋዮቹ አንደበት”፤ የሚሉ ጥያቄዎችን ያካተተ ቃለ-መጠይቅ እና ኢትዮጵያ በልማት መገስገሷና ብሩህ ዘመን እንደሚጠብቃት የሚገልጽ ቪዲዮ በ”ሳክርድ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ” ተዘጋጅቶ በወንጌል ዶት ኮም በኩል ተበትኗል። ከአስተያየቶቹ መካከል የሚከተሉት በጎ ግን እውነታን ያላገናዘቡ መልሶች ይገኙባቸዋል፦

  • መንፈሳዊ በረከት ብቻ ሳይሆን…ምድራዊ፣ ማቴሪያል በረከት፣ የዝናብ በረከት፣ የፖለቲካ በረከት
  • ብዙ ማእድናት አሉን፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች እስከሚነሱ ድረስ እግዚአብሔር ጠብቋቸዋል
  • በሠላሳ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ የዛሬዋን ጃፓንን ትሆናለች

የደራሲ ደመወዝ መጽሐፍና የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች የቪዲዮ ምልልሶች መቀናበር በአጋጣሚ ነው ወይስ ታቅዶ ነው? በጎ ምኞት ጉዳት የለበትም ቢባልም፣ ቤተክርስቲያን ዘላለማዊውን የፍትህ ወንጌል የመስበክ ሥልጣኗን እንዳትቀማ ሰሞነኛ ጉዳዮችን ከማስተጋባት መቆጠብ ይኖርባታል፤ ከወንጌል ንጽህና ጋር በማይጣጣም አኳኋን ተመሳስላ መኖር አይቻላትምና። የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ እንጂ ሰው ሊሆን አይችልም። የሥልጣን ሁሉ ምንጭ የሆነው ኃያል አምላክ በሥልጣን ላይ ለጊዜው ላስቀመጣቸው ልትጸልይና የወንጌልን እውነት ልታሳውቃቸው ቤተክርስቲያን ተጠርታለች። ያም ፍትህና ሰላም እንዲሰፍን ነው፤ ወንጌል እንዲሮጥ፣ ለሰዎች ደህንነት እንዲሆን ነው። በየትኛውም ዘመን መንግሥታት ቤተክርስቲያንን ለዓላማቸው ለማሠለፍ ያልሞከሩበት ጊዜ የለም። አልገዛ ያለውን ያሳድዳሉ፤ ወይም በማግባባት ያንኑ ያሰቡትን ዕቅዳቸውን ያስፈጽማሉ። ቁም ነገሩ የዘመኑን መንፈስ መለየት መቻሉ ላይ ነው። ለዚህም የሚበቃ የክርስቶስ ጸጋ አለ።

 

Read 677201 times Last modified on Thursday, 17 November 2011 21:24

122008 comments

  • Comment Link fghjxfn Wednesday, 04 February 2026 01:48 posted by fghjxfn

    Устали заставлять себя работать силой? Включите сакральный поток и не работайте больше не дня.

    Когда каждый шаг требует невозможных усилий.

    -человек генератор дизайн человека;
    -генератор это в дизайне человека;
    -генератор тип личности;
    -дизайн человека генератор;
    -дизайн человека генератор кто это;
    -генератор тип личности дизайн человека;
    -генератор по дизайну человека;

  • Comment Link onlinecasino Wednesday, 04 February 2026 01:44 posted by onlinecasino

    Sponsor announcements, commercial partnerships and deals covered

  • Comment Link emergency auto glass replacement affordable charlotte nc Wednesday, 04 February 2026 01:43 posted by emergency auto glass replacement affordable charlotte nc

    refreshing depth of insight. I found myself fully engaged from start to

  • Comment Link hdcneeh Wednesday, 04 February 2026 01:40 posted by hdcneeh

    Хватит инвестировать свой ресурс в мусор. Ваш мотор заведен для чужой поездки.

    Фрустрация — это крик вашего тела.

    -тип личности генератор дизайн;
    -генератор тип личности дизайн;
    -человек генератор дизайн человека;
    -тип личности генератор;
    -человек генератор кто это;
    -тип личности генератор это;

  • Comment Link ArielDuels Wednesday, 04 February 2026 01:39 posted by ArielDuels

    Wonderful facts. Regards.
    best canadian online casino zodiac casino canada online casino canada

  • Comment Link Koumyou.Boo.Jp Wednesday, 04 February 2026 01:27 posted by Koumyou.Boo.Jp

    This particular weblog is absorbing. Topics including this
    are frequently neglected, if perhaps truth be told. Mostly the most excellent of
    the Online world seriously isn't the most widely marketed subject material,
    but rather all things other than them, the unnoticed herd with
    personal blogs that are simply significantly more suitable as opposed
    to the ones of essential influencers. This is this type of a weblog.
    My husband and I will certainly provide recommendations, sometimes whenever not
    motivated to do it. First is, keep on authoring. Second is, always keep penning constantly.
    Third is, employ your own blog page to grow your very own approach.
    I am not a blog writer per se; I am actually a Postpartum Massage Therapist.
    I practice Postpartum Massage Therapy, being able to help women of all ages to recover following having a baby.
    It's fulfilling work. That is exactly what I devote the majority of my precious time undertaking, though I have additionally treasured posting from the moment I was a teen. I am
    a well-read individual and every year or so I browse a pile way taller when compared with myself personally.
    hahaha In the subsequent twelve months, could be I could get really serious concerning blogging and site-building.

    The thing is, it cannot simply a design; the efforts of penning
    and posting habitually makes a blogging site expand in some amount of time.

  • Comment Link car window replacement emergency charlotte nc Wednesday, 04 February 2026 01:15 posted by car window replacement emergency charlotte nc

    Comment 64: This blog post is truly outstanding and provides such a

  • Comment Link DEBET Wednesday, 04 February 2026 01:11 posted by DEBET

    Với giao diện thân thiện và đa dạng sản phẩm giải trí, DEBET mang lại trải nghiệm cá cược khá thuận tiện. Nền tảng này phù hợp với người chơi ưu tiên sự an toàn và thao tác nhanh gọn. http://debetus.com/

  • Comment Link onlinecasino Wednesday, 04 February 2026 01:07 posted by onlinecasino

    Champions League livescore updates, follow your favorite European clubs in real time tonight

  • Comment Link auto glass replacement charlotte nc auto glass replacement near 28289 Wednesday, 04 February 2026 01:02 posted by auto glass replacement charlotte nc auto glass replacement near 28289

    create an experience that feels both educational and inspiring. Every

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.