ርዕሰ አንቀጽ
መሬት መሬት ሲያይ
አምስት ብር መንገድ ላይ ወድቆ ያገኘ አንድ ወጣት፣ ሌላም አገኝ እንደሆን ብሎ መሬት መሬቱን ሲያይ ረጅም ዓመታት አሳለፈ። በዓመታቱ መካከል ይኸው ወጣት ብዙ ነገር ለቃቀመ። ሃያ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ አሥራ ስድስት አዝራሮችን፣ ሃምሳ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት የማስታወቂያ መርፌ ቁልፎችን እና አሥራ ሁለት ሳንቲም ለቀመ። ወፍራም መቀነት የማያስታግሰው የወገብ ህመምና ንፉግነትን አተረፈ። መሬት መሬት ሲያይ፣ አንድም ቀን ቀና ብሎ የማለዳ ፀሐይ ጮራዋን ስትፈነጥቅ ወይም የወዳጆቹን ፈገግታ ሆነ የአበቦችን ፍካታ ሳያይ ኖረ። መሬት መሬት እያዩ መጓዝ ኪሳራው የከፋ ነው። ምድር ላይ መኖር የራሱ ግዴታ ቢኖርበትም፣ ከምድር ጋር እንዲህ መቆራኘት፣ ማንነትን እና አቅጣጫን ማሳቱ አይቀርም።
This post is extremely useful!
Your ideas are on point!
Very polished writing.
Amazing job simplifying this topic!
This was a great read!
A smart and meaningful post.
Very helpful and beautifully written.
You write with real talent!
Short but powerful. Great job!
Sharp points, great delivery.