×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 42
Sunday, 13 November 2011 21:04

ያለ ዕውቀት መቅናት Featured

Rate this item
(0 votes)

የሚከተለው ርዕሰ አንቀጽ፣ ማኅበረ በኵር ካሳተመው፣ ከጮራ መጽሔት ቁጥር 34፣ ገጽ 1-2 ላይ የተወሰደ ሲሆን፣ ለብዙዎች እንዲዳረስ በማሰብ ለጥፈነዋል። ይህን ጽሑፍ ያዘጋጁትን ወገኖች እግዚአብሔር ይባርካቸው።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፣ አሜን።

ያለ ዕውቀት መቅናት

ቅንአትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብሎ ለሁለት ከፍሎ ማየት የተለመደ ሆኗል። ሥጋዊ ቅናት በጥቅሉ ሲታይ፣ በሌላው ሰው ማደግና አንዳች ነገር ማግኘት ደስ አለ መሰኘትና የሌላው ይሆን ዘንድ ያልወደዱትን ለራስ ለማድረግ መፈለግ በመሆኑ ፍቺው ብዙም አያደናግርም። በመንፈሳዊ ስም የሚጠራው ቅናት ግን ሁል ጊዜ መንፈሳዊ ነው ለማለት ይቸግራል። እንዲያውም መንፈሳዊ ካባ የደረበ ሥጋዊ ቅናት ሆኖ የሚገለጥበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም።

እንዲህ ያለውን መንፈስ ለበስ ሥጋዊ ቅናት ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ‘ያለ ዕውቀት መቅናት’ ይለዋል። ይህን ያለውም የዘመዶቹን የአይሁድን ቅንአት ምንነት በገለጸበት ክፍል ነው። እነርሱ ለእግዚአብሔር የሚቀኑ መሆናቸውን ሐዋርያው አልሸሸገም፤ ለእግዚአብሔር የቀኑ ይሁኑ እንጂ፣ ቅንአታቸው በዕውቀት ላይ ስላልተመሠረተ የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም በመፈለግ ለእግዚአብሔር ጽድቅ መገዛትን እንቢ አሉ [ሮሜ 10፣13]።

እንዲህ ባለው ቀናተኛነት ውስጥ ጳውሎስ የተባለው ሳውልም ዐልፏል። ለሙሴ ሕግ በመቅናት እግዚአብሔርን ያገለገለ እየመሰለው የክርስቶስን ተከታዮች በጽኑ ያሳድድ ነበር። በክርስቶስ ወደ ማመን ከተመለሰ በኋላ፣ በትዝታ ወደ ኋላ ተመልሶ በአይሁድ መካከል የሰጠው ምስክርነት ይህንኑ ያስረዳል። “እኔ … የአባቶቼንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፣ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ነኝ። ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰርሁ ወደ ወኅኒም አሳልፌ እየሰጠሁ ይህን መንገድ [ክርስትናን] እስከ ሞት ድረስ አሳደድሁ” [የሐዋርያት ሥራ 22:3-4]። እንዲሁም ለፊልጵስዩስ ምእመናን በጻፈው መልእክቱ፣ “ስለ ቅንአት ብትጠይቁ፣ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤” ብሏል [3:6]። ምናልባትም ይህ በዘመኑ አይሁድ ዘንድ የቀናተኛነት ጣሪያ ተደርጎ ሳይወሰድ አልቀረም። ምክንያቱም ጳውሎስ ‘በቅንአትም ቢሆን እኔን የሚበልጥ ማንም የለም’ እያለ ነውና የሚናገረው [ቁ.4]። ይህ ሁሉ ግን፣ የሙሴ ሕግ የተሰጠው ፍጹም የሆነው [ወንጌል] እስኪመጣ ድረስ መሆኑን ካለማወቅ የመጣ ዐጕል ቅናት እንደ ሆነ ለመገንዘብ አያስቸግርም። ያለ ዕውቀት መቅናት ይሏል ይህ ነው።

ጳውሎስ ይህንና የመሳሰለውን ኢመንፈሳዊ ድርጊት ክርስትና ላይ ቆሞ ሲያስታውሰው፣ እንደ መልካም ሥራ ሳይሆን “እንደ ጕድፍ”፣ “እንደ ጕዳት”ም ነው የቆጠረው [ቁ.7-9]። ምክንያቱም ጌታ በወንጌል፣ “እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከምንም በላይ ደግሞ የሚገላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል” [ዮሐንስ 16:1-2] በማለቱ፣ እንዲህ ያለው ቅንአት፦ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን እንጂ የማያስደስት ቅንአት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርና ምስጋናን የሚያሰጥ ሳይሆን በኀጢአተኛነት የሚያስጠይቅና ኵነኔን የሚያስከትል ቅንአት፣ እንዲያው በጥቅሉ ባዶ ቅንአት መሆኑን አስተውሏል።

ዛሬም እንደ አይሁድ ለእግዚአብሔር በመቅናት ስም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚመላለሱ ሞልተዋል። በዘመናችን ለእናት ቤተ ክርስቲያን ህልውና ቀንተው የተነሡ ብዙዎች፣ ቅንአታቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው ያላቸው ፍቅር በራሱ ደስ የሚያሰኝ ነው ሊባል ቢችልም፣ ቅንአታቸውን የሚያሳዩበት መንገድ ግን በአብዛኛው ክርስቲያናዊናመንፈሳዊ ሆኖ አይታይም፤ በዕውቀት ላይ ስላልተመሠረተም ከአይሁድ ቅንአት የተለየ አይደለም።

ቅንአታቸው በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ላይ በተመሠረተ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመራ አለ መሆኑ ዋናው መሠረታዊ ችግር ተደርጎ ይወሰዳል። ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድምድራዊት ድርጅት በመቍጠር፣ ህልውናዋን የእግዚአብሔርን ቃል በጥራት በማስተማር ሳይሆን በምድራዊ ጥበብና በሥጋዊ ኀይል ለማስጠበቅ ላይ ታች ይላሉ። የቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በወንጌሉ ቃል ሳይሆን ማለቂያ በሌለው፣ የአሮጊቶችን ተረት በመሰለ ትምህርት እንዲሞላ ለማድረግ ይታገላሉ። ቤተ ክርስቲያን በቃለ እግዚአብሔር ወልዳ ያሳደገቻቸውንና ደረሱልኝ ብላ ተስፋ የጣለችባቸውን አገልጋዮቿን፣ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን፣ መልካሙን ክፉ፣ ክፉውን መልካም፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውን ጣፋጭ [ኢሳይያስ 5:20] በማለት የተለያየ ስም እያወጡ ያሳድዳሉ። በሌሎች አስታከው ወንጌልንና የወንጌል እንብርት የሆነውን ኢየሱስን ይቃወማሉ። ውስጣዊ ዐይኖቻቸው በርተው እነዚህንና ሌሎችንም ክፉ ሥራዎቻቸውን፣ ለእግዚአብሔር በእውነት ቀንተው ስሙን ካስከበሩት እውነተኛ አገልጋዮቹ ሥራ ጋር ቢያስተያዩት ምንኛ ባፈሩ! ድርጊታቸውንም እንደ ጳውሎስ ጕዳትና ጕድፍ አድርገው በቆጠሩት ነበር።

ከመንፈሳዊ ቅንአት አንጻር፣ ከላይ ከተዘረዘሩት ክፉ ሥራዎች መካከል አንዱ ስንኳ ለእግዚአብሔር መቅናትን ማሳያ ሆኖ ሊጠቀስ አይችልም። ቤተ ክርስቲያን የገሃነም ደጆች የማይችሏት ሆኖ በክርስቶስ የተመሠረተች የእግዚአብሔር መንግሥት እንጂ፣ በሰዎች ስምምነት የተቋቋመች ምድራዊ ድርጅት ወይም “ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር” አይደለችምና ጠባቂዋ ራሱ ጌታ እግዚአብሔር መሆኑ በቅድሚያ መታወቅ አለበት። የሥልጣኗና የትምህርቷ መሠረት፣ የህልውናዋ መጠበቂያም ሌሎች የፈጠራ ጽሑፎች ሳይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ምክንያት መሰደድ እንጂ ማሳደድ ከክርስቶስና ከሐዋርያቱ የተማረችው፣ የተቀበለችውም ግብሯ አይደለም። የወንጌልን ማእከላዊ መልእክት ክርስቶስን በመስበክ የምሥራቹን ቃል ታበሥራለች እንጂ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ክርስቶስንና ወንጌሉን አትቃወምም።

አይሁድ ለሙሴ ሕግ ቀንተው ክርስቶስን በመስቀላቸው፣ ተከታዮቹ ሐዋርያትንም ተቃውመው እስከ ሞት ድረስ በማሳደዳቸው እግዚአብሔርን አሳዘኑት እንጂ ደስ አላሰኙትም። “እነርሱ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፤ እኛንም አሳደዱን፣ እግዚአብሔርንም ደስ አላሰኙትም፤ የሰውም ሁሉ ፀር ሆኑ፤ ይኸውም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ለመከልከል ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኀጢአታቸውን ሁል ጊዜ በራሳቸው ላይ እስከ መጨረሻው እያከማቹ ይሄዳሉ። ቁጣውም በእነርሱ ላይ ያለ ልክ መጥቶአል” [1ኛ ተሰሎንቄ 2:15-16፤ ዐ.መ.ት.]። ስለዚህ በአይሁድ መንገድ ቀናተኛ የሆኑ ሁሉ፣ እንደ ጳውሎስ ጌታንና ቤተ ክርስቲያንን ከማሳደድ ተመልሰው ስለ ጌታ ስም ለመሰደድ ራሳቸውን ካላዘጋጁ፣ ስለ ገፉት የእግዚአብሔር ጽድቅና ስለ ፈጸሙት ኀጢአት፣ በዚህ ዓለም በተለያየ መከራና ችግር ይቀጣሉ፤ በመጨረሻው ቀንም ይጠየቁበታል።

ሰላም ሊሰጣት የመጣውን ጌታን በመቃወም ሰቅላ ለገደለችው፣ ወደ እርስዋም የተላኩ ነቢያትን ላሳደደችው ለኢየሩሳሌም በራሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ነቢያትን የምትገድል፣ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፉችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! [እናንተ ግን] አልወደዳችሁምም። እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል” [ማቴዎስ 23:37-38] ተብሎ እንደ ተነገረባት፣ በ 70 ዓ.ም. ሮማውያን አወደሟት፤ ብዙ አይሁድም ዐለቁ።

ዛሬም ያለ ዕውቀት “ቀናተኛ” የሆኑ ሁሉ፣ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር በመቅናት ስም ከፈጸመችው ዐመፅና ዐመፅዋ ካስከተለባት ከዚህ ጥፋት መማር አለባቸው። ለእግዚአብሔር ቀንተናል በሚል እግዚአብሔርን ሲቃወሙ እንዳይገኙ ሊጠነቀቁ ይገባል። ለሰላማቸው የሚሆነውን የክርስቶስን ወንጌል መቃወማቸውንና የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሯቸውን ማሳደዳቸውን የሚገፉበት ከሆነ ግን፣ የዘላለም ሕይወት እንዳይገባቸው በራሳቸው ላይ ፈርደዋል ማለት ነው [የሐዋርያት ሥራ 13:46]።

Read 624520 times

128204 comments

  • Comment Link Vivod iz zapoya v Krasnodare_bpKl Wednesday, 01 April 2026 08:49 posted by Vivod iz zapoya v Krasnodare_bpKl

    вывод из запоя круглосуточно вывод из запоя круглосуточно .

  • Comment Link Vivod iz zapoya na domy _toSl Wednesday, 01 April 2026 08:41 posted by Vivod iz zapoya na domy _toSl

    реабилитация наркоманов реабилитация наркоманов .

  • Comment Link zakazat kyhnu_boPa Wednesday, 01 April 2026 08:38 posted by zakazat kyhnu_boPa

    заказать кухню рассчитать стоимость zakazat-kuhnyu-11.ru .

  • Comment Link Flepvlimjap Wednesday, 01 April 2026 08:24 posted by Flepvlimjap

    Okay, buddy, I accidentally discovered something shockingly creative, I had to stop everything and tell you.

    This thing is a pixel miracle. It’s packed with crazy layouts, creative magic, and just the right amount of mad energy.

    Still don’t believe me? Alright, take a peek right here!

    Need more hype? Fine. Imagine a robot designer dreamed of a site after arguing with ChatGPT. That’s the frequency this content gives.

    So don’t be shy, and tattoo the link. Because real talk, this is what your brain craved.

    That’s it.

  • Comment Link Vivod iz zapoya v Krasnodare_dokt Wednesday, 01 April 2026 08:17 posted by Vivod iz zapoya v Krasnodare_dokt

    вывод из запоя цена вывод из запоя цена .

  • Comment Link Cveti nedorogo_djpl Wednesday, 01 April 2026 08:12 posted by Cveti nedorogo_djpl

    недорогой букет цветов http://cveti-nederogo.ru/ .

  • Comment Link Vivod iz zapoya na domy _ytMi Wednesday, 01 April 2026 08:08 posted by Vivod iz zapoya na domy _ytMi

    лечение наркомании vyvod-iz-zapoya-na-domu-samara-1.ru .

  • Comment Link casino bonus Codes No deposit 2022 Wednesday, 01 April 2026 08:02 posted by casino bonus Codes No deposit 2022

    canada no deposit bonus casino, gambling statistics
    australia 202 and online slots australia paypal, or best online casino sites canada

  • Comment Link Vivod iz zapoya na domy _uzsl Wednesday, 01 April 2026 08:01 posted by Vivod iz zapoya na domy _uzsl

    капельница от запоя капельница от запоя .

  • Comment Link Vivod iz zapoya na domy _ldSl Wednesday, 01 April 2026 07:54 posted by Vivod iz zapoya na domy _ldSl

    вывод из запоя на дому вывод из запоя на дому .

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.