ስጦታህን እወቅ
እግዚአብሔር ስጦታ ሰጥቶኛል? ስጦታዬስ ምንድነው? የተፈጥሮ ችሎታዬን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው ማለት እችላለሁ? ስጦታ ያድጋል አያድግም? … ሌሎች ሌሎች ጥያቄዎች ይኖሩህ ይሆናል። ረጋ ብለህ እያስተዋልክ ይህንን ጽሑፍ ካነበብክ ማን ያውቃል መልስ ታገኝ ይሆናል።
እያንዳንዱ ክርስቲያን አንድ ወይም ከዚያ የበለጠ ስጦታ አለው
በክርስቶስ ደም በተዋጀው ቤተሰብ ውስጥ እያንዳንዱ በእግዚአብሔር ቃል የተወለደ ሕጻን ስጦታ ተቀብሏል። “ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ እያንዳንዳችሁ እያሳስበናል (1ኛጴጥ. 410)። እያንዳንዱ ክርስቲያን ስጦታውን የማወቅና የማሳደግ ኃላፊነት አለበት። ልክ እንደ ዘር ወይም አዲስ እንደ ተወለደ ሕጻን መንፈሳዊ ስጦታዎችም ከትንሹ ይጀምሩና በጥንቃቄ ከተያዙ ያድጋሉ። በፍቅርና በመንፈስ ቅዱስ በመመካት ሳናቋርጥ ከተጠቀምንባቸው ግባቸውን የሚመቱ ጠንካራ መሣሪያዎች ይሆናሉ። ስጦታውን ባሳደገ መጠን የእግዚአብሔር ባሪያ ራሱ ጠቃሚ ሰው መሆን ይጀምራል። ስጦታው ከተቀባዩ አኳኋን፣ ባሕርይና ካለፈበት ልምምድ ጋር ይስማማል። ስጦታው የወደ ፊት ኑሮውን እንኳ ሊወስን ይችላል። ምክንያቱም ስጦታዎቹ መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱ ክርስቲያን በሕይወት ዘመኑ ሊፈጽማቸው የሚገባቸውን ሥራዎች የሚያሳዩ ጠቋሚዎች ስለሆኑ ነው። ስጦታ ላንተ በግልህ የሚያስደስትህና ስሜት የሚያሳድርብህ የራስህ ስጦታ ምን ምን መሆኑን ለይተህ ስታውቅ ነው። ስጦታህን ለማወቅ ከሚረዱህ ነገሮች አራት ያህል እንጠቅሳለን።
በተፈጥሮ ችሎታህ ጀምር፣ በዚያ ግን አትቁም
የተፈጥሮ ችሎታና መንፈሳዊ ስጦታ አንድ ባይሆኑም እንኳ የተያያዙ ነገሮች ናቸው። እንድ ሰው እንዳለው ስጦታዎቹ “… በውስጥ የተደበቀ የተፈጥሮ ችሎታን ይጠቁማሉ”። እንግዲህ ስጦታን ለማወቅ ከሚደረጉ የመጀመሪያ እርምጃዎች አንዱ የተፈጥሮ ችሎታን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጠቀም መጀመር ነው። በዚህ ዓይነት መንገድ አንዱን ስጦታዋን ያወቀች አንዲት ሴት አውቃለሁ። ፍቃዱ ኦርጋንና ፒያኖ የመጫወት ችሎታ አለው። በአምልኰ ጊዜ፣ በወጣቶች ስብሰባና በሌሎችም ስብሰባዎች መጫወት ይወዳል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት ሰዎች ሙዚቃውን ከመውደዳቸውም በላይ ሌላም የሚናገሩት ነገር አለ። የአምልኰ የመክፈቻ መዝሙር ሲጫወት አእምሮዬ ወደ እግዚአብሔር ይመለሳል። ከዚያም መንፈሴ ለአምልኰ ይዘጋጃል። የሙዚቃውን ቃላት እከተላለሁ፤ ጌታም በዚያ ውስጥ ለልቤ ይናገራል። እንግዲህ የመንፈሳዊ ስጦታን አንድ መለኪያ በጸሎት ይመነዝሩታል። በእምነት ላይ በተመሠረተ ጽኑ ጸሎት አንጻር ያስቀምጡታል። ይኸም ጸሎት እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን እንዲሰጠን አንዴ ጠይቀነው የጠየቅነውን ነገር ለማግኘት በትዕግስት የምንጠባበቅበት ጸሎት መሆኑን የእግዚአብሔር ሰዎች ይናገራሉ። ለእግዚአብሔር አንዴ

